"በበጀት ዓመቱ በቢሮው ታቅደው ያልተከናወኑ ተግ...

image description
- In ንግደረ    0

"በበጀት ዓመቱ በቢሮው ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀሪ ጊዜያት ለማከናወን ሁላችንም ርብርብ ልናደርግ ይገባል!" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ

"በበጀት ዓመቱ በቢሮው ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀሪ ጊዜያት ለማከናወን ሁላችንም ርብርብ ልናደርግ ይገባል!" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ

ግንቦት 26፣ 2018 ዓ.ም.

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከቢሮው ፕሮሰስ ካውንስል አባላት ጋር የቢሮውን አጠቃላይ አፈጻጸም ገምግመዋል። በግምገማው ዘርፎችና ዳይሬክቶሬቶች በከተማችን ፍትሃዊ፣ ዘመናዊ እና በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል ያከናወኗቸውን ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ተገምግሟል።

በግምገማው ላይም ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ባለፉት የበጀት ዓመቱ አስራ አንድ ወራት በአዲስ አበባ ፍትሃዊ፣ ዘመናዊ እና በውድድር ላይ የተመሰረተ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻልና የከተማችን ነዋሪዎችን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ በሁሉም ዘርፎች እና ዳይሬክቶሬቶች የተከናወኑ ተግባራት በጎ እና አበረታች መሆናቸውን ገልጸው፣ በቀጣይም በበጀት ዓመቱ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀሪው ጊዜ ሁላችንም በተጠናከረ ርብርብ ማከናወን እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments