በግብይት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በመፍታት የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባ ተገለፀ።
በግብይት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በመፍታት የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት እያረጋገጡ መሄድ እንደሚገባ ተገለፀ።
ግንቦት 27/2018 ዓ ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በከተማችን አዲስ አበባ የገበያ ማዓከላት ውስጥ ከሚገኙ አምራች አርሶ አደሮች ጋር በወቅታዊ የምርት አቅርቦት እና የግብይት ሂደት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በገበያ ማዕከላት ከአቅርቦት፣ ከግብይትና ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ የሚታዩ ክፍተቶች እና ጠንካራ ጎኖች በቢሮው የገበያ ማዕከላት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ከአቅርቦትና ከግብይት አንፃር የታዩ ሰው ሰራሽ ክፍተቶችን በማንሳት ችግሮቹ በሚፈቱበት ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
እንደ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ የከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ውድነትን ለመከላከልና የግብይት ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ቢልዮኖችን በማውጣት የገበያ ማዕከላትን በመገንባትና የተለያዩ አሠራሮችን በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በገበያ ማዕከላቱ በቂ ምርት በማስገባት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በመጨረሻም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በግብይት ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን በመፍታት የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ከአምራቾች ጋር በቅርበት መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments