"በከተማችን የሚካሄዱ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉ...

image description
- In ንግደረ    0

"በከተማችን የሚካሄዱ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ስራዎች ነጋዴውን ወደ ህጋዊ ስርዓት የሚያስገቡ እንጂ ከንግድ ስራዓቱ ውጪ እንዲሆኑ የሚያደርጉ መሆን የለባቸውም" የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ

"በከተማችን የሚካሄዱ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ስራዎች ነጋዴውን ወደ ህጋዊ ስርዓት የሚያስገቡ እንጂ ከንግድ ስራዓቱ ውጪ እንዲሆኑ የሚያደርጉ መሆን የለባቸውም" የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ

ሰኔ 01/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ የ11 ወራት እቅድ አፈፃፀምን በመገምገም ለቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። በግምገማ መድረኩ ላይ የዘርፉ የ11 ወራት አፈፃፀም ቀርቦ፣ በንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስመኘው ተሾመ ሰፊ ማብራርያ ተሰጥቶበታል።

በውይይት መድረኩ ላይ ከከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ ቡድን መሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በአፈፃፀም ወቅት ያጋጠሟቸውን ጠንካራና ደካማ ጎኖች አንስተው በመድረክ ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የውይይት መድረኩን ማጠቃለያ የሰጡት የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በከተማችን የሚካሄዱ የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ስራዎች ነጋዴውን ወደ ህጋዊ ስርዓት የሚያስገቡ እንጂ ከንግድ ስራ ውጪ እንዲሆኑ የማድረግ ዓላማ እንደሌላቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የንግድ ድርጅቶች ህግና ስርዓትን ጠብቀው እንዲሰሩ በቅርበት ሆኖ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን አውስተው፣ በድጋፍ አሰጣጥ ወቅት ህጋዊ ሆነው የማይሰሩ የንግድ ድርጅቶችን ወደ ህጋዊነት የመመለስ ስራ ሊሰራ ይገባል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments