የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሁናዊ ስኬቶች፣ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአዲስ ሚዲያ ጋር በመተባበር የእንጠያየቅ መርሃ-ግብር አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አሁናዊ ስኬቶች፣ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከአዲስ ሚዲያ ጋር በመተባበር የእንጠያየቅ መርሃ-ግብር አካሄደ።
ሰኔ 04/2018 ዓ ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነትን ለመከላከል ያከናወናቸው ተግባራት ከመድረክ ከቀረበ በኋላ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ቀርቦ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ከአስረአንዱም ክ/ከተማ ከነዋሪው የተወከሉ ተሳታፊዎች በንግድ ዘርፉ ይታያሉ ያሏቸውን የአጸፃፀም ክፍተቶች በማንሳት የቢሮው አመራሮችን ጠይቀዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በዋርካ የእንጠያየቅ መድረክ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት ምላሽ መንግስት ከመቼውም ጊዜ በላይ የንግድ ስርዓቱን ለማዘመንና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች በኑሮ ውድነት እንዳይጉዱ የተለያዩ አሠራሮችን በመዘርጋት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ከግብይት አንፃር በነፃ ገበያ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ ክፍቶችን ታሳቢ በማድረግ ነፃ ገበያውን ከመደገፍ ባሻገር የተለያዩ ምርቶችን በገበያ ማዕከላትና በእሁድ ገበያዎች ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በመጨረሻም ከነዋሪዎች የተነሱ ጥያቄዎችን በመውሰድ የአፈፃፀም ክፍተቶችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments