"በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን በማ...

image description
- In ንግደረ    0

"በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የግብይት ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል"። ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

"በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የግብይት ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል"። ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ

ሰኔ 8/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ከተማ የገበያ ማረጋጋትና ህገ-ወጥ ንግድ ቁጥጥር የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ግብረ-ሃይል በከተማችን አዲስ አበባ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊና የግብርረ-ሀይሉ ምክትል ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በቀጣዮቹ ሦስት ወራት የሚከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ከመድረክ ዕቅድ አቅርበዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ባቀረቡት ዕቅድ ላይ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት የምርት አቅርቦትን እንዲሁም የሰንበት ገበያዎችን ቁጥር በማሳደግና የቁጥጥር ስርዓቱን በማጠናከር የተረጋጋ የግብይት ስርዓት መፍጠር የዕቅዱ ዋና ግብ መሆኑን ገልፀዋል።

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌተናል ጄነራል አስራት ዴነሮ፣ የአዲስ አበባ ፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የክ/ከተማና የወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች፣ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች የግብረ-ኃይሉ የከተማ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ዕቅዱ ከቀረበ በኋላ በግብይት ስርዓቱ ውስጥ ይታያሉ የተባሉ ክፍተቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

የግብረ-ኃይሉ ሰብሳቢና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ በመድረኩ በሰጡት ሀሳብ በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የግብይት ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነትን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።

አቶ ጃንጥራር አያይዘውም አመራሩ በከተማችን የሚገኙ የገበያ ማዕከላትን፣ የእሁድ ገበያዎችን፣ የህብረት ስራ ማህበራት በቂ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ በቅርብ ሆኖ ሊደግፍና ሊከታተል ይገባል ብለዋል።

ክቡር አቶ ጃንጥራር በግብይት ስርዓት ውስጥ የሚታዩ ብልሹ አሠራሮች በቀጥታ በህዝቡ ላይ ጫና የሚያሳርፉ መሆናቸውን በመግለፅ ህገ-ወጥነት ተግባር ላይ በሚሳተፍ ማንኛውም አካል ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ሊሄድ ይገባል ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments