በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሠራሮችንና የሥነ-ምግባር ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ተጠየቀ።
በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሠራሮችንና የሥነ-ምግባር ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎውን እንዲያጠናክር ተጠየቀ።
ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የፀረ-ሙስናና የሥነ-ምግባር ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ከድጃ መሐመድ፣ በ2018 በጀት ዓመት ሥነ-ምግባርን ከማስፈንና ሙስናን ከመከላከል አንፃር የተሠሩ ሥራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ዳይሬክተሯ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ቢሮው በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ የሙስናና የሥነ-ምግባር ችግሮች ምንጮችን ቀድሞ በመለየት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የመከላከል ሥራ ማከናወኑን ገልጸዋል።
በተግባር የተፈጸሙ የሥነ-ምግባር ጥሰቶችን መሠረት በማድረግም አስፈላጊው ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን አስረድተዋል።
ቢሮው የሥነ-ምግባርና የሙስና ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል ባከናወነው ሥራ ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ማዳን መቻሉንና ሊጭበረበር የነበረ የ212 ሚሊዮን ብር የባንክ ስሊፕ እንዳይጭበረበር ማድረግ መቻሉን ወ/ሮ ከድጃ ገልጸዋል።
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፣ በነዳጅ ማደያዎች፣ በገበያ ማዕከላትና በሰንበት ገበያዎች የተፈጸሙ የሥነ-ምግባር ጥሰቶችን በመመርመር ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ተወስደዋል። በተጨማሪም ለህብረተሰቡ የማሳወቅ ሥራ ተከናውኗል።
ቢሮው የሙስናና የሥነ-ምግባር ችግሮችን ለመቀነስ ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት በመሥራትና በተለያዩ አማራጮች ጥቆማዎችን በመቀበል ተገቢውን ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ በየጊዜው እየወሰደ መምጣቱን ዳይሬክተሯ አውስተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት የሙስናና የሥነ-ምግባር ችግሮችን በትርጉም ያለው መልኩ ለመቀነስ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ወ/ሮ ከድጃ መሐመድ ገልጸዋል።
ዳይሬክተሯ ህብረተሰቡ ቀደም ሲል ሲያደርግ የነበረውን የነቃ ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል። በተለይም በዘርፉ የሚያጋጥሙ ብልሹ አሠራሮችን በ8588 ነፃ የስልክ መስመር ወይም በአካል በመገኘት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments