የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2018 ዓ ም የሥራ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2018 ዓ ም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የንግድ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2018 ዓ ም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የንግድ ጽ/ቤት አመራሮች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ።

ሀምሌ 21/2018 ዓ ም

በመድረኩ የ2018 ዓ ም በጀት አመት አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የንግድ ዘርፍ ስራዎችን በላቀ ሁኔታ ለማስፈፀም 24/7 ሲሰራ መቆየቱን ገልፀዋል፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በበጀት ዓመቱ በንግድ ዘርፍ የተሠሩ ስራዎች ውጤታማ በመሆናቸው ቢሮው በአፈፃፀም ከፍተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ መቻሉን አሳውቀዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓትን ዲጂታላይዝ ማድረግ በመቻሉ 706ሺ 855 የሚሆኑ የኦንላይን አገልግሎቶችን መስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡

እንደ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ገለፃ ቢሮው ከአጎራባች ክልሎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በማቅረብ የዋጋ ግሽበትና የኑሮ ዉድነትን ማረጋጋት ተችሏል፡፡

የግብይት ስርዓት ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ የንግድ ህገ-ወጥነትን መከላከል አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በበጀት ዓመቱ በ223,760 የንግድ ድርጅቶች የበር ለበር ቁጥጥር በማደረግ 24,568 ጥፋተኛ ነጋዴዎችን በመለየት እንደ ጥፋታቸው ዓይነትና ክብደት 24,568 ህጋዊና አስተዳራዊ የእርምት እርምጃ በመዉሰድ 20,617 ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በነባር ገበያ ማዕከላት ማስፋፊያ ከማድረግ ባሻገር የሰሚት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከል ግንባታውን በማጠናቀቅ ስራ እንዲጀምር ማድረግ የተቻለ መሆኑን በመግለፅ ይህም በከተማችን አዲስ አበባ የዘመናዊ ገበያ ማዕከላት ብዛትን ወደ ሰባት አሳድጎታል ብለዋል፡፡

ከገበያ ማእከላት ባሻገር በበጀት አመቱ ተጨማሪ 37 የሰንበት ገበያዎችን ወደ ስራ በማስገባት በከተማችን አዲስ አበባ የሰንበት ገበያ መዳረሻዎችን 256 ማድረስ የተቻለ ሲሆን ይህም የከተማችን ነዋሪዎች የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በየአካባቢያቸው እስከ 20 በመቶ በሚሆን ቅናሽ መሸመት መቻላቸው የኑሮ ውድነት በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ከተሳታፊዎች በአፈፃፀም ሂደት የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተነስተው የቢሮው አመራሮች ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ በሰጡት ማጠቃለያ የቢሮውን የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በላቀ ደረጃ በማስፈፀም ከተማችን አዲስ አበባ ፍትሃዊ የግብይት ስርዓት የሰፈነባት ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች ተቀናጅተው 24/7 መስራት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments