የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በ20...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በ2018 ዓ ም በጀት ዓመት በምርት አቅርቦትና ገበያ በማረጋጋት ዙሪያ አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ከቆዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይትና የዕውቅና መድረክ አካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በ2018 ዓ ም በጀት ዓመት በምርት አቅርቦትና ገበያ በማረጋጋት ዙሪያ አስተዋፅኦ ሲያበረክቱ ከቆዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይትና የዕውቅና መድረክ አካሄደ።

ሀምሌ 27/2018 ዓ ም

በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የፍጆታ ምርቶች በአራቱም አቅጣጫዎች ወደ ከተማችን በማስገባት ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ሰኬታማ ሰራ መሰራቱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመደረኩ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር ቢሮው በበጀት ዓመቱ የምርት አቅርቦትን በማሳደግና የደላሎችን ጣልቃ ገብነት በመከላከል ረገድ አመርቂ ሰራ በመሰራቱ የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

ከመድረክ የ2018 በጀት ዓመት የምርት አቅርቦትና ግብይት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

ከመድረክ በቀረቡ ጥያቄዎች ዙሪያ የቢሮው ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ባስተላለፉት መልዕክት ምርት አቅራቢዎችና አርሶ አደሮች ምርቶችን በቀጥታ ወደ ገበያ ማዕከላት በማስገባትና የደላሎችን ጣልቃ ገብነት በማስወገድ ገበያውን በማረጋጋት ረገድ የበኩላቸውን ሚና አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ምርት አቅራቢ ተሳታፊዎች ከቢሮ ኃላፊዎች የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸው መድረኩ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments