የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግዱና ከሸማቹ ማህበ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግዱና ከሸማቹ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መሰራቱ የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገለፀ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግዱና ከሸማቹ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ መሰራቱ የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገለፀ።

ነሀሴ 05/2018 ዓ ም

የአዲስ አበባ ንግድ ማህበራትና ዘርፍ ምክር ቤት እንዲሁም የሸማቾች ጥበቃ ማህበር አመራሮች ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጋር ተቀራርበው በሚሰሩበት ሁኔታ ላይ በመመካከር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

በመድረኩ ማህበራቱ የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ በሰሯቸው ስራዎች ዙሪያ ውይይት በማካሄድ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል።

ቢሮውን በመወከል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ ከማህበራቱ ተወካዮች ጋር የስምምነት ሰነዱን ተፈራርመዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግድና ሸማች ማህበረሰብ ጋር ተቀራርቦ ሲሰራ የቆየ መሆኑ እና ይህን ግንኙነት በአሠራር አጠናክሮ ማስቀጠል የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments