ቢሮው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለዘርፍ አመራሮች ካስኬድ በማድረግ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
ቢሮው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለዘርፍ አመራሮች ካስኬድ በማድረግ የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
ነሀሴ 11/2018 ዓ ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የቢሮውን የ2019 ዓ ም በጀት ዓመት ዕቅድ ለዘርፎች ካሰኬድ በማድረግ ከዘርፍ አመራሮች ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ የስምምነት ሰነድ ፊርማ መርሀ-ግብሩ ከተከናወነ በኋላ ባደረጉት ንግግር ቢሮው የ2018 ዓ ም በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገበ ቢሆንም ከህዝቡ እርካታ አንፃር አሁንም ብዙ መልፋት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በተያዘው በጀት ዓመት እንደ አመራር ስራዎችን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመምራት የህዝቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments