"የዳቦ ፋብሪካዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው የዳ...

image description
- In ንግደረ    0

"የዳቦ ፋብሪካዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው የዳቦ አቅርቦትን በማሳደግ በዝቅተኛ ገቢ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽነታቸውን ይበልጥ ሊያሳድጉ ይገባል" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ:- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ።

"የዳቦ ፋብሪካዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው የዳቦ አቅርቦትን በማሳደግ በዝቅተኛ ገቢ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽነታቸውን ይበልጥ ሊያሳድጉ ይገባል" ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ:- የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ።

ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም

በከተማችን አዲስ አበባ ከመንግስት ለ10 ዓመት ኮንትራት መሬት ወስደው ዳቦ በማምረት ላይ የሚገኙ የዳቦ ፋብሪካዎች በገቡት ውል መሠረት ህብረተሰቡን እያገለገሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በተካሄደ የዳሰሳ ጥናት ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የዳቦ ፋብሪካ ባለቤቶች በተገኙበት የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት የቀረበ ሲሆን በምርት ሂደት የታዩ ችግሮችና ጠንካራ ጎኖች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የዳሰሳው ዓላማ ዓላማ ዳቦ ፋብሪካዎች ያሉባቸውን ችግሮች በመለየት መፍትሄ ለመስጠት መሆኑን ከመድረክ ተገልጿል።

በውይይቱ ማጠቃለያ ሀሳባቸውን የሰጡት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ "የዳቦ ፋብሪካዎች ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው የዳቦ አቅርቦትን በማሳደግ በዝቅተኛ ገቢ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽነታቸውን ይበልጥ ሊያሳድጉ ይገባል ብለዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ አያይዘውም በዳሰሳ ጥናቱ የተለዩ ክፍተቶችን በመውሰድ ማስተካከል እንደሚገባ ገልፀው ለዚህም ቢሮው ቀጣይነት ያለው የቅርብ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል።

በመጨረሻም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የበገቡትን ውል መሠረት በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ የዳቦ ፋብሪካዎች የምስጋና ሰርተፊኬት ከክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እጅ ተቀብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments