የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2019 ዓ.ም ዘመን...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀመረ።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ባዛር በይፋ አሰጀመረ።

ነሀሴ 28/2018 ዓ ም

የበዓል ባዛሮቹ በ11ዱም ክ/ከተሞች የተዘጋጁ ሲሆን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበላ እና ሌሎች የከተማችን ከፍተኛ አመራሮች ባዛሮቹን በይፋ አስጀምረውታል።

በቂርቆስ ክ/ከተማ የተካሄደውን የአዲስ ዓመት በዓል ባዛር መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ በከተማችን አዲስ አበባ የዋጋ ንረትን ከመከላከል እና የንግድ ስርዓቱን ፍትሃዊነት ከማረጋገጥ አንፃር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወኑን ገልፀዋል።

የፍጆታ አቅርቦት ችግር አለመኖሩን የገለፁት አቶ ፀጋዬ በዓልን እንደ ሰበብ በማድረግ በምርት ላይ አግባብነት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ፣ ምርት በሚያከማቹና በሚደብቁ ላይ መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳ ብለዋል።

አቶ ፀጋዬ አያይዘውም የዘንድሮውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በተከፈቱ ባዛሮች ላይ በቂ ምርት መቅረቡን ገልፀው የከተማው ነዋሪ በባዛሮቹ ተገኝቶ እንዲገበያይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንደ አቶ ፀጋዬ ገለፃ ቢሮው በየወቅቱ የሚያዘጋጃቸው የበዓል ባዛሮች በበዓል ወቅት ሊከሰት የሚችልን የዋጋ ንረት በመከላከል ገበያውን በማረጋጋት ረገድ የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

የበዓል ባዛሮቹ ከዛሬ 28/12/18 ጀምሮ እስከ ጷግሜ 5/2018 ዓ ም ለህብረተሰብ ክፍት ሆነው አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ተገልጿል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments