የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የእመርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ሁለገብ የገበያ ማዕከል የተለያዩ መርሃ-ግብሮችን አከናወነ።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የእመርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በኮልፌ ሁለገብ የገበያ ማዕከል የተለያዩ መርሃ-ግብሮችን አከናወነ።
ጷግሜን 01/2018 ዓ ም
የ2019 የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ አምስቱን የጷግሜ ቀናት መካከል የዛሬው የእመርታ ቀንን ከአምራቾችና ከአርቲስቶች ጋር በመሆን በኮልፌ ሁለገብ የገበያ ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
ቀኑን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የግብይት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ደበሌ በአገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ አመታት በተሠሩ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች ከጥገኝነት አዙሪት በመውጣት ወደ አምራችነት ልዕልና ተሸጋግረናል ብለዋል።
እንደ አቶ ፀጋዬ ገለፃ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የከተማ አስተዳደሩ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር በወጪ በማድረግ ስድስት ዘመናዊና ሁለገብ የገበያ ማዕከላት በመገንባት አጠቃላይ የገበያ ማዕከላቱን ቁጥር ወደ ሰባት በማሳደግ የከተማችንን የግብይት ስርዓት ፍትሃዊና የተረጋጋ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ፡፡
እነዚህ የገበያ ማዕከላት ከተማችን አዲስ አበባን ዘመናዊና ፍትሃዊ የንግድ ስርዓት የሰፈነባት ስሉጥ ከተማ ለማድረግ የተያዘውን ራዕይ ለማሳካት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
የገበያ ማዕከላቱ ተገንብተው ወደ ስራ በመግባታቸው በከተማችን አዲስ አበባ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ ከማዕከላቱ አልፎ በእሁድና ቅዳሜ ገበያዎች በቂ ምርት እንዲኖር ባማድረግ ህብረተሰቡ የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የከተማችን ታዋቂ ሴት አርቲስቶች አበባ አየወሽ በመጨፈርና የግጥም መርሃ-ግብር በማቅረብ ለበዓሉ ድምቀት ሰጥተውታል።
በመድረኩ የኮልፌ ሁለ-ገብ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል ሸማቾችን እና አመራቾችን በማገናኘት የዋጋ ንረትን በመከላከል ረገድ ሚናው የላቀ መሆኑ ተገልጿል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments