ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ለከተማችን ሸማቾች የአትክልት፣ የፍራፍሬ እና የሰብል ምርቶቾን በማቅረብ ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ለከተማችን ሸማቾች የአትክልት፣ የፍራፍሬ እና የሰብል ምርቶቾን በማቅረብ ገበያውን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
መስከረም 12/2018 ዓ ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ ሰባት የገበያ ማዕከላት የላፍቶ ሁለገብ ዘመናዊ የገበያ ማዕከል አንዱ ሲሆን ማዕከሉ የከተማችንን ገበያ በማረጋጋት ረገድ የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የገበያ ማዕከላት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ሀሰኑ የላፍቶ ገበያ ማዕከል የአትክልት ፍራፍሬና የሰብል ምርቶችን ለሸማቹ ማህበሰሰብ ከመደበኛው ነፃ ገበያ እስከ 20% ቅናሽ በማቅረብ የከተማችንን ገበያ በማረጋጋት ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አቶ ሽመልስ አያይዘው የላፎቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል ከወፍጮ ጀምሮ የባንክ፣ የቁጠባ፣ የኩዊንስ ሱፐር ማርኬት፣ ካፌና ሬስቶራንት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎትችን በአንድ ላይ አካቶ የያዘ ሁለገብና ዘመናዊ የገበያ ማዕከል መሆኑን ገልፀዋል።
በላፍቶ ሁለገብ የገበያ ማዕከል አምራች አርሶ አደሮች ምርታቸውን በቀጥታ ይዘው የሚቀርቡ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለምዶ አትክልት ተራ እየተባለ በሚጠራው ቦታ የነበሩ ነጋዴዎች የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለሸማቹ በቅናሽ የሚያቀርቡበት መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ሽመልስ በመጨረሻም የከተማ አስተዳደሩ በቢልዮኖች ብር በመመደብ በከተማችን አራቱም አቅጣጫዎች ሰባት የገበያ ማዕከላትን ገንብቶ የተለያዩ የአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የሰብልና ሌሎች የፍጆታ ምርቶችን ከመደበኛው ገበያ አሰከ 20% ቅናሽ በማቅረብ ገበያውን ከማረጋጋት አልፈው አዲስ አበባ ፍትሃዊና ዘመናዊ የግብይት ስርዓት የሰፈነባት ከተማ እንድትሆን ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments