ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የጀመሩትን የሪፎርም ስራ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ በክብርት አዳነች አቤቤ በድጋሚ ተሾሙ።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ሆነው የጀመሩትን የሪፎርም ስራ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ በክብርት አዳነች አቤቤ በድጋሚ ተሾሙ።
ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የተሰጣቸውን ኃላፊነት ከተማችን አዲስ አበባን ዘመናዊና ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት የሰፈነባት ስሉጥ ከተማ የማድረግ ራዕያችንን ለማሳካት የአገልግሎት አሠጣጡን በቴክኖሎጂ በማዘመን፣ የገበያ መሠረተ-ልማቶችን በማሟላት፣ የምርት እጥረት እንዳይኖር በማድረግና የዋጋ ንረትን በመከላከል ረገድ ብቃት ያለው አመራር መስጠታቸውን ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተገልጿል።
ወ/ሮ ሀቢባ የከተማችንን የንግድ ሥርዓት በማዘመን ረገድ የጀመሩትን የሪፎርም ሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ በድጋሚ ቢሮውን በኃላፊነት እንዲመሩ መሾማቸውን ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
በዛሬው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ምስረታ ላይ በድጋሚ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ በመሾምዎ የቢሮው ሠራተኞችና አመራሮች እንኳን ደስ ያለዎት በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments