ተቋሙን ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ለማጽዳት በሚያ...

image description
- In code inforcement    0

ተቋሙን ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ለማጽዳት በሚያካሂደው እንቅስቃሴ ጥፋተኛ በሆኑ አካላት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ  ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም   
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በ2017 በጀት  የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ተቋሙን ከሌብነትና ብልሹ አሰራር ለማጽዳት በጀመረው እንቅስቃሴ  በኦንላይን ሲሰጡ የነበሩ አገልግሎቶችን ኦዲት በማድረግ ተጠያቂነት ማስፈኑን አስታወቀ። 
ጉዳዩን አስመልክቶ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ፍሰሃ ጥበቡ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ቢሮው ከወረዳ ጀምሮ ባለው መዋቅር በ1200 ባለሙያዎች አማካኝነት  አካውንቶ ከፈቶ ሲሰጥ የነበሩትን የኦንላይን አገልግሎቶችን በደ ከተማ መዋቅር በመሳብ ለቁጥጥር አመቺ በሚሆን ደረጃ በ26 ባለሙያዎች ከአንድ ማዕከል ግልጋሎቱ እንዲሰጥ በማድረግ እና ቀደም ባሉ አካውንቶች የተሰጡ አገልግሎቶችን ትክክለኛነት የማረጋገጥ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹት ምክትል ቢሮ ኋላፊው አቶ ፍስሀ ጥበቡ በዚህም ማጣራት 339 ሃሰተኛ አካውንቶች በቢሮው ስም ተከፈተው ህገወጥ አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበር ማረጋገጥ መቻሉን አብራርተዋል፡፡
 በእነዚህ ሃሰተኛ አካውንቶች 430 ከንግድ ዘርፍ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች መሰጠታቸውንና በዚህ ሂደት ውስጥ የተሳተፉ 131 ፈጻሚዎችና አመራሮች ተጠያቂ ማድረጉን እና ግልጋሎቶችንም ህገ-ወጥ በሆነ አግባብ ባገኙ የንግድ ድርጅቶችና ተቋማት ላይም አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ቢሮው በኦዲት የለያቸውን ችግር ለመፍታት አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን ከወረዳና ከክፍለ ከተማ ወደ ማእከል በማምጣት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ያብራሩት አቶ ፍስሀ ይህም የኦንላይን አገልገሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ለቁጥጥር አመቺ ማደረጉን ነው ገልጸዋል፡፡
በቀጣም መሰል ህገ-ወጥ አካውንቶች እንዳይከፈቱ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ትክኖሎጂውን ይበልጥ ማዘመን እና የአገልግሎት ኦዲቱም ቀጣነት ባለው አግባብ በማስኬድ በሚገኙ ጉድለቶች ላይ ቢሮው የተጠናከረ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎችን በሁሉም ጥፋተኞች ላይ መውሰዱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments