የቢሮው በ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም...

image description
- In code inforcement    2

የቢሮው በ2017 የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም የተሻለ ውጤት የታየበት መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም መልካም ጅምሮች ማስመዝገቡ ችላል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ፣ኢንደስትሪ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ።
ይህ የተገለፀው ቋሚ ኮሚቴው በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም በገመገመበት መድረኩ ነው። 
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር አቶሜ አበበ ቢሮው በ2017 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት ያደረገው ጥረት የተሻለ ነው ብሏል።
የኦላይን አገልግሎት  ከብልሹ አሰራር ለማፅዳት ፣የምርቶች ዋጋ ለማረጋጋትና  የእሁድ ገበያዎችን በማጠናከር የኑሮ ውድነት ጫናዎችን ለማቃለል የተከናወኑ ተግባራት ጥሩ ውጤት የታየባቸው ናቸውም ብለዋል።
ከዚህም ባሻገር ህገወጥነትን ለመከላከል የተሰራው ስራ ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉ ተናግረዋል   ፡፡
አክለውም የመንደር ንግድ ቁጥጥር ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት የታዩ ለውጦች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተናግረዋል።
በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ለቀጣይ ወራቶች የሚስተካከሉ ስራዎች ወስደን እንሰራልብለዋል።
ቅንጅታዊ ስራዎችን እና የውስጥ ሰራተኞችን በስልጠና አግዘን ቢሮውን እንቀይረዋለን  ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments