
የገና በዓል የምርት አቅርቦትን በሚመለከት የቅድመ ዝግጅ ስራው ያለበትን ደረጃ እና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ
ቢሮው የገና በዓል የምርት አቅርቦት ዝግጅት ያለበትን ደረጃ በሚመለከት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ፡፡
===========================
አዲስ አበባ ታህሳስ 14ቀን 2017ዓ.ም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የገና በዓል የምርት አቅርቦትን በሚመለከት የቅድመ ዝግጅ ስራው ያለበትን ደረጃ እና በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ በከተማዋ ምርት አቅርቦትን ከሚመሩና ከሚከታተሉ ባለድርሻአካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ በመደበኛነት መቅረብ ከሚገባቸው ምርቶች በተጨማሪ በቀጣይ ሳምንታት የሚከበረው የገና በዓል የምርት ፍላጎትን የሚጨምር መሆኑን ታሳቢ በማድረግ ሁሉም ክፍል ከተሞች፤ ከተማ ኮሚሽን፤ ኢንዱስትሪ፤ህብትረ ስራ ኮሞሽን እና ንግድ ቢሮ የሚያስተዳድራቸው የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት የሰብል ምርቶች፤ አትክልት እና ፍራፍሬ፣ የቁም እንስሳት፤ዶሮ፤ እንቁላል እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽዎ ምርቶችን በስፋት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ በሚቻልባቸው አግባቦች ላይ በስፋት ውይይጥ ተደርጓል፡፡
አቶ ፍስሃ ጥበቡ የንግድ ግብይትና ገበያ ልማት ምክትል ቢሮ ኃላፊ በውይይቱ ወቅት ሁሉም የገበያ ማዕከላት እና የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በምርት አቅርቦቱ ላይ በርትተው በመስራት የምርት ዕጥረት እንዳይፈጠር እና የዋጋ መጨመር እንዳያጋጥም ጥብቅክትትል እና ድጋፍ ማድረግ በየደረጃው ካለው አመራር እና ባለሙያ የሚጠበቅ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ውይይቱን የመሩት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ከክፍለ ከተማ ኃለፊዎችና ከማዕከል ሴክተር ተቋም መሪዎች የተነሱ ሀሳቦችን ባጠቃለሉበት ወቅት እንደገለጹት ቀደም ብሎ በባዕላት ወቅት እንደሚደረገው ሁሉም የቅዳሜና ዕሁድ ገበያዎች በዓሉ ሲቃረብ ሰፋ ላሉ ቀናት ምርቶችን የሚያቀርቡ መሆኑን ዕና በመቸረሻዎቹ የበዓል ዋዜማ ቀናት በማዕከል ያሉ ሴክተር ተቋማት፣ አምራቾች እና ምርትን በጅምላ የሚያስመጡ አከፋፋዮች ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርቡባቸው የበዓል የምርት አቅርቦት ባዛሮች በሁሉም ክፍለ ከተሞች በቂ ዝግጅት መደረጉን እንዲሁም ዛሬ ከተደረገው ውይይት መነሻ እና ከቀረቡ ሪፖርቶች አሁን ላይየምርት አቅርቦቱ የተሸለና እጥረት ያለመኖሩን በመጥቀስ ይህንኑ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚሀገባም አሳስበዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments