የገና በዓል አስመልክቶ የተለያዩ አምራች ኢንተር...

image description
- In ንግደረ    0

የገና በዓል አስመልክቶ የተለያዩ አምራች ኢንተርፕራዞች በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አውቶብስ ተራ ከረሚላ ህንፃ አካባቢ ኢግዚቪሽንና ባዛር በይፋ ተከፈተ፡፡

መጭውን የገና በዓል አስመልክቶ የተለያዩ አምራች ኢንተርፕራዞች የሚሳተፉበት የገና ኢግዚቪሽንና ባዛር  በይፋ ተከፈተ፡፡
***********************
አዲስ አበባ ንግዲ ቢሮ ታህሳስ 22-2017ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ አውቶብስ ተራ ከረሚላ ህንፃ አካባቢ የተከፈተውን ባዛር የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ፣ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩ፣ የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራ ክህሎት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሰለማዊት ከበደ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መሀመድ ሊጋኒ አስጀምረውታል:: የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ እንዳሉት የበዓል ሰሞንን አስመልክቶ የምርት እጥረት እንዲሁም የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ባዛሩ ወሳኝነት አለው ሲሉ ተናግረዋል:: የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ መስጠፋ ትኩ ባዛሩ ኢንተርፕራይዞች ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ በመፍጠር ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል:: ባዛሩ እስከ በዓሉ ዋዜማ የሚቆይ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ ሰላማዊት ለሸማቹ ማህ/ሰብ አማራጭ ገበያ ከመሆን ባለፈ ኢንተርፕራይዞችም ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያስተዋውቁበት ጠቃሚ ባዛር ሲሉ  ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማትና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ዘርፍ ሃላፊ አቶ መሀመድ ሊጋኒ በበኩላቸው በዛሬው ቀን በ11ዱም ክ/ከተማ ባዛር እየተከፈተ መሆኑን ገልፀው ባዛሩ ኢንተርፕራይዞችን የገበያ ትስስርና ምርታቸውን ለህብረተሰቡ የሚያስተዋውቁበትና ለኢንዱትሪ ሽግግሩ አቅም የሚፈጥሩበት መሆኑን ተናግረዋል::


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments