የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገና ባዕልን አ...

image description
- In ንግደረ    0

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገና ባዕልን አስመልክቶ የከተማ ግብርና የእንስሳት ተዋፅኦ የኢንዱስትሪ ምርቶችና በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት ኢግዚቪሽንና ባዛር በይፋ ተከፈተ፡፡

የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የገና ባዕልን አስመልክቶ የከተማ ግብርና የእንስሳት ተዋፅኦ የኢንዱስትሪ ምርቶችና  በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት ባዛር ተከፈተ::

***********************

በልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ፅህፈት ቤት ፣ህብረት ስራ ማህበርና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት እንዲሁም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ  አካላት ጋር በመሆን በተቀናጀ መልኩ ባዛሩ ተከፍቷል ።
ባዛሩን በማስከፈት ግብይቱን የጎበኙት የልደታ ክክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በጉብኝቱ ወቅት እንደ ተናገሩት ከበዓል ጋር ተያይዞ የህብረተሰቡ ፍላጎት ከፍተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የእሁድ ገበያና የሸማች ማህበራት በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶችን በማቅረብ ነዋሪውን ያማከለ ግብይት እንዲኖር አስተዳደሩ የተሻለ ስራ ሲሰራ ቆይቷል በማለት አሁን ያለው የምርት አቅርቦት በበቂ ሁኔታና በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረብን ገልፀው ህብረተሰቡ በመጠነኛ ዋጋ ምርቶች እንዲገዛ ይረዳል ብለዋል ወ/ሮ አበባ አያይዘው ከክፍለ ከተማ  እስከ ወረዳ ድረስ በበአል ሸመታው ወቅት በምርቶች ላይ ከፍተኛ  የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና የምርት እጥረት እንዳያጋጥም የግብይቱን ስርአት የተሳለጠ ለማድረግ በቅንጅት በመስራት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል በማለት ገልፀዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ እንደተናገሩት በበዓላት  ወቅት የሚስተዋለውን የግብይት የዋጋ ግሽፈት ና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የሚያስችል ለተከታታይ (6) ቀናት የሚቆይ  ባዛር በዛሬው ዕለት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ወረዳዎች ባዛሩን መከፈቱን ገልፀው በንግድ ባዛሩ ትስስር የተፈጠረላቸው ጅምላ ነጋዴዎች፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ የተፈቀደላቸው የወረዳ ሸማች ማህበራት የእሁድ ገቢያ ተሳታፊ ነጋዴዎች የገቢያ ማረጋጋት ተግባሩ እስከ በዓል ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
ዶ/ር አክለው ባዛሩ አቅርቦትና ግብይት ስርዓቱ የታለመለትን ዋጋ የማረጋጋት እና ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ  ዋጋ ምርት የማቅረብ ሂደቱ ተጠናክሮ እስከ ዋዜማ ድረስ ይቀጥላል  በማለት በባዛሩ የግብርና የእንስሳት ተዋእፆ የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚሸጥ  ገልፀዋል።
ማህበረሰቡም የምርት አቅርቦት በተመጣጣኝ ዋጋ እየተከናወነ በሚገኘው የንግድ ባዛሮች በመሄድ የሚፈልገውን መሸመት ይችላል!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments