
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤትና የክፍለ ከተማው ህብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠር የዋጋ ንረት እና የምርት አቅርቦት እጥረትን ለማስቀረት ባዛር ተከፈተ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤትና የክፍለ ከተማው ህብረት ስራ ማህበራት ጽ/ቤት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጠር የዋጋ ንረት እና የምርት አቅርቦት እጥረትን ለማስቀረት ባዛር ተከፈተ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ እንደተናገሩት በክፍለ ከተማው ህብረተሰቡ በበዓላት ወቅት የሚፈጠርበትን የዋጋ ጫና ለማስቀረትና በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ከማድረግ ባሻገር የገበያ መዳረሻ ቦታዎችን በማስፋት ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል የክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም ክብረት በበኩላቸው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በልዩ ሁኔታ ቅቤ ፣ እንቁላል ፣ የዘይት ፣የባልትና ውጤቶች፣የቡና፣የጤፍ እና የስንዴ ምርቶች በበቂ ሁኔታ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረተሰቡ የሚቀርቡ መሆኑን ገልጸዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ደራርቱ ኦሊቃ በክፍለ ከተማው በ10ሩም ወረዳዎች 15 የባዛር ቦታዎች ለመጪው በዓላት የኢንዱስትና የግብርና ምርቶችን ለሸማች ማህብረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መቅረቡን ገልጸዋል።
በወረዳና በክፍለ ከተማ የንግድ ግብረ ሃይሉ የቁጥጥር ስርዓቱን አጠናክሮ እንደሚገኝ ገልጸው ህብረተሰቡ ያለ አግባብ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ሲያጋጥመው ለሚመለከተው የህግ አካል የማሳወቅ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
ህብረተሰቡ የኑሮ ውድነቱን እና ገበያውን ለማረጋጋት የቀረቡትን የተለያዩ የምርት አይነቶች ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ቅናሽ ልዩነት ስላለው በሚቀርበው የባዛር ቦታ በመገኘት መጠቅም እንዲሚችል ተገልጿል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments