ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ተሳታፊዎች እውቅናና ሽልማት ተበረተላቸው።
ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ተሳታፊዎች እውቅናና ሽልማት ተበረተላቸው።
==========================
አዲስ አበባ ታህሳስ 24/2017 ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ዛሬ በኢሊሊ ሆቴል የምርት አቅርቦት ለገበያ መረጋጋት በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም በቅዳሜና እሁድ ገበያ ላይ ለተሳታፊ ነጋዴዎች፣ አምራቾችና አቅራቢዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ኃላፊ የቅዳሜና እሁድ ገበያ ከተጀመረበት ግዜ አንስቶ እየሰፋ የሄደና ተደራሽነቱን ያረጋገጠ ሆኗል ያሉ ሲሆን ገበያው የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት፣ የከተማውን ዝቅተኛ እና መካከለኛ የማህበረሰብ ክፍል የአቅርቦት እና የዋጋ ንረት ችግር እየፈታ የሚገኝ ነው ብለዋል፡፡
ባለፉት አመታት በተካሄደው ገበያውን የማስፋት እንቅስቃሴ ከግብይት ስርዓቱ ከደላላ ትስስር ነፃ ሆኖ በገበያ ስርዓት የማመራ እንዲሆን ለማድረግና በውስን ቦታዎች የነበረውን የገበያ ቦታ ዛሬ በ197 ቦታዎች ላይ ተደራሽ ለማድረግ የተቻለ ሲሆን በውስጡም ከ1800 በላይ ነጋዴዎች እየተሳተፉበት እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባና የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ባስተላለፉት መልክት የቅዳሜና የእሁድ ገበያዎች በማንኛውም ግዜ የማይናወጥ አቋም ያላቸው ገበያ ተደራሽነት የነበራቸው መልካም ዜጎች ናቸው ብለዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ከዘርፉ አስፈላጊነት አንፃር የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረው የተጀመሩ መልካም ተሞክሮዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም የቅዳሜና እሁድ ገበያ ላይ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ነጋዴዎች፣ አምራቾች፣ አቅራቢዎች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የእውቅናና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments