
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአራዳ ክፍለ ከተማ ለገና በዓል የተዘጋጀውን ባዛር ጎበኙ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአራዳ ክፍለ ከተማ ለገና በዓል የተዘጋጀውን ባዛር ጎበኙ፡፡
===========================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በአራዳ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ለገና በዓል የተዘጋጀውን ባዛር ከክፍለ ከተማው አመራሮች ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
ወ/ሮ ሀቢባ በገና ባዛሩ ላይ ተዘዋውረው ሲጎበኙ የቀረቡ የግብዓት አይነቶችን በተለይም የግብርና ምርቶችና የኢንዱስትሪ ምርቶች ከመደበኛው ገበያ የዋጋ ቅናሽ የታየበትና ብዙ የምርት አይነት የቀረበ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ሸማቹ ማህበረሰብ በተዘጋጀው ባዛር የበዓል ግብዓቶችን ሳይቸገር ማግኘት የሚችልባቸው ብቻ ሳይሆን ሰፊ የዋጋ ቅናሽ የሚያገኝበት እንደሆነ ኃላፊዋ በጉብኝታቸው አውስተዋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ የተዘጋጀው የገና በዓል ባዛር እስከ ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች በቅዳሜና እሁድ ገበያ ሲደረግባቸው የነበሩ ቦታዎች ላይም የግብይት አቅርቦቱ እንደቀጠለ መሆኑና መግዛት ለሚፈልግ ሰው የተመቻቸለት መሆኑን የአራዳ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላይ ሙሉጌታ መረጃውን ሰጥተውናል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments