ለመጪው የገና በዓል የተለያዩ እንስሳት በስፋት...

image description
- In ንግደረ    0

ለመጪው የገና በዓል የተለያዩ እንስሳት በስፋት ወደ አቃቂ የከብት ገበያ እየገቡ ይገኛል።

ለመጪው የገና በዓል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የእርድ እንስሳት በስፋት ወደ አቃቂ የከብት ገበያ እየገቡ ይገኛል።

አዲስ አበባ ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም

የአዲሰ አበባ ከተማ አሰተዳደር ንግድ ቢሮ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በአቃቂ የከብት ገበያ በመገኘት የአርድ እንስሳት ገበያ ያለበትን ሁኔታ ቅኝት አድርጓል።

በቅኝታችን በገበያው የቁም እንስሳት በበቂ ሁኔታ መቅረባቸውን መመልከት ተችሏል ፡

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በላይ ደምሴ ጽ/ቤቱ ለገና በዓል ዕቅድ ይዞ ወደ ስራ በመግባት በሁሉም ዘርፍ በቂ አቅርቦት በማስገባት የተረጋጋ ገበያ መፍጠር መቻሉን አንስተው የእርድ እንስሳት አቅርቦት እስከ በዓሉ ዋዜማ ድረስ በበቂ ሁኔታ የሚኖር መሆኑን በመጥቀስ ማህበረሰቡ ህጋዊ የእርድ ስርዓቱን ብቻ በመጠቀም እርድ እንዲፈጽም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የአቃቂ የከብት ገበያ አስተባባሪ አቶ ደበበ ለማ በገበያ ማዕከሉ ለበዓሉ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የእርድ እንስሳት በስፋት እየገቡ እንደሚገኝ ገልፀው ማህበረሰቡ የሚፈልገዉን አማራጭ በአቅራቢያዉ እንዲያገኝ በስፋት አቅርቦት ላይ እንደተሰራ ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments