
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በከተማዋ ነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭትን በተመለከተ መረጃ ሰጠ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በከተማዋ ነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭትን በተመለከተ መረጃ ሰጠ፡፡
አዲስ አበባ ታህሳስ 27 ቀን 2017ዓ.ም
ንግድ ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ ተሽከርካሪዎች እና ነዳጅን ለሚጠቀሙ የኮንስትራክሽንና ተያያዥ ማሽኖች በሚቀርበው የነዳጅ አቅርቦት እና ስርጭትን በሚመለከት በዛሬው ዕለት መረጃን አጋርቷል፡፡ ቢሮው በመረጃው እንደገለጸው የከተማዋ ዕለታዊ የነዳጅ ፍላጎት 1.4 ሚሊዮን ሊትር መሆኑን እና ይህንን አቅርቦት ለማሟላት በሚያስችል መልኩ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር መስሪያቤት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን በዚህ በጀት ዓመት ዕለታዊ ፍላጎትን የሚመጥን የነዳጅ አቅርቦት መኖሩን እና ይህንንም መረጃ በየዕለቱ ለተጠቃሚዎቹ በትስስር ገጾቹ ላይ እየገለጸ መሆኑን አብራርቷል፡፡
ሰሞኑን በከተማዋ የነዳጅ ማደያዎች የተሸከርካሪዎች ሰልፍ መኖሩን ገልጾ የዚህም መነሻው በየዕለት የሚቀርበው የነዳጅ መጠን መቀነስ አለመሆኑን አንስቶ በከተማዋ 125 ማደያዎች ሲኖር 118 በተጨባጭ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
በመሆኑም የተሸከርካሪ ሰልፎቹ መነሻ አቅርቦት እጥረት ሳይሆነ ስርጭቱ ጋር በተያያዘ ቤንዚን የጨረሱ እና ያዘዙ 46 ማደያዎች፣ ናፍጣ 72 ማደያዎች ያዘዙ ሲሆን በከተማዋ አገልግሎት ከሚሰጡ118 ማደያዎች 68 ላይ ቤንዚን መኖሩን እንዲሁም 46 ማደያዎች ላይ ደግሞ ናፍጣ በመሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡ በጥቅሉም በዛሬው ዕለት ከሚያስፈልገው 1.4 ሚሊዮን አቅርቦት ቤንዚን 1.77 ሚሊዮን ሊትር እና 1.08 ሚሊዮን ሊትር ናፍጣ በማደያዎች ያለ በመሆኑ ተገልጋዮች አቅርቦት ያለባቸውን ማደያዎች ከንግድ ቢሮ ትስስር ገጾች ላይ በመከታተል መጠቀም እንደሚችሉ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments