
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸ ላይ ውይይት አካሄደ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸ ላይ ውይይት አካሄደ
አዲስ አበባ ጥር 8 ቀን 2017ዓ.ም
ንግድ ቢሮው በዝግጅ ምዕራፍ መከናወን የነበረባቸውን ተግባራት በተሻለ መልኩ መፈጸም መቻሉን በዚህም ዕቅድን ለሚመለከታቸው አካላት ማወያየትን ጨምሮ በተለያ ርዕሶች ላይ 587,446 የንግዱና ሸማች ማህበረሰብ ግንዛቤ ፈጥሯል፡፡ ከዋና ዋና ተግባረት አንጻርም ከንግድ ምዝገባና ዕድሳት አንፃር 31,267 በመፈፀም የእቅዱን 100% በላይ በማከናወን፣ 46,002 አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት 53,576 የእቅዱን 100% ማከናወኑ፣ 411,548 የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 285,622 በመፈፀም የእቅዱን 69.4% ሲሆን አፈፃፀሙም ዝቅ ያለበት ዋና ምክንያት የገቢዎች ክሊራንስ ባለማግኘታቸው ሲሆን ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ከሚመለከተው አካት ጋር በመነጋገር የ15 (አስራ አምስት) ቀን የዕድሳት ጊዜ ማራዘም መደረጉ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱ እንዲያጥር በማድረግ አቅርቦትን በማሳለጥ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ የሚያስችሉ 217 የእሁድ ገበያ መዳረሻዎች ወደ ተግባር ሲገቡ ከንግድ ቁጥጥርና ክትትል አኳያም በ225‚306 የንግድ ድርጅቶች ላይ የበር ለበር ክትትል ቁጥጥር በማድረግ የንግድ ህገ-ወጥነትን ለመከላከል የታቀደ ሲሆን 255‚228 (100% በላይ)፣ 131,250 የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ማህደሮችን ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ 158‚803 (ከ100% በላይ) ኦዲት በማድረግ፣ በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን እና የነዳጅ ስርጭት ቁጥጥሩም የተሻለ መሆኑ ተመለክቷል፡፡
በሌላ በኩል ለስራ ምቹ አካባቢን የመፍጠር፣ የተግባቦትና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራግን መግታት ፣ የሻማቾች መብት ማስተበቅ እና ህገ ወጥ የዋጋ ንረትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ቢሮው አመርቂ ውጤት ያሳየባቸው መሆኑ ተነስቷል፡፡ በውይይቱ ከወረዳ እስከ ማዕከል የሚገኙ አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን በውይይቱ ማጠቃለያም የቢሮው ምክትል ኃለፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ እና የርብርባችን ማዕከል ሊሆኑ ይገባል ባሏቸው ነጥቦች ላይ ዝርዝር ሰሃቦችን በማቅረብ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments