ከሲዳማ ክልል ለመጡ አርሶ አደሮች የመሸጫ ሱቆች...

image description
- In ንግደረ    0

ከሲዳማ ክልል ለመጡ አርሶ አደሮች የመሸጫ ሱቆችን አስተላለፈ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ጥር 9/2017 ዓ.ም

ከሲዳማ ክልል ለመጡ አርሶ አደሮች የመሸጫ ሱቆችን አስተላለፈ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተገነቡ የመሸጫ የገበያ ማዕከላት ውስጥ 113 (አንድ መቶ አስራ ሶስት) ሱቆችን ለሁሉም ክልሎች ለመስጠት ቀደም ብሎ በተደረሰው መግባባት መሰረት በዛሬው ዕለት ከሲዳማ ክልል ለመጡ አምራቾች ሱቆችን አስተላልፏል፡፡

ቢሮ ዛሬ ለሲዳማ ክልል የተደለደለለትን የመሸጫ ሱቆች ቁልፍ ባስረከበበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለፁት ሸማቹንና ነጋዴውን በቀጥታ ለማገናኘት እና ህገ-ወጥ ደላላን በመቁረጥ ጤናማ የንግድ እንቅስቃሴን ለመፍጠር አስተጽዎ እንዳለው ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊዋ አዲስ አበባ የሁሉም ናት የሚለውን አስተሳሰብ የበለጠ እንደሚያጎላው ተናግረዋል፡፡

የመሸጫ ሱቆችን ቁልፍ የተረከቡት የሲዳማ ክልል ተወካዮች እና ነጋዴዎች እንዳሉት አዲስ አበባ የሀገራችን ዋና መዲና ከመሆኗ ባሻገር የብዝሀንነታችን መገለጫና የሁላችንም ከተማ መሆኗን አረጋግጠናል ያሉ ሲሆን ተገቢውን ምርት በማቅረብ የከተማውን ማህበረሰብ ለመጥቀም ዝግጁነታቸውን ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments