"ግብረ ሀይሉ ህገወጥነትን ለመከላከል፣ ገበያውን...

image description
- In ንግደረ    0

"ግብረ ሀይሉ ህገወጥነትን ለመከላከል፣ ገበያውን ለማረጋጋትና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሰራ ይገባል"

አቶ ጃንጥራር አባይ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገበያ ማረጋጋት፣ ገቢ መሰብሰብ፣ ህገወጥ ንግድ ቁጥጥር የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ግብረ ሀይል የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የግብረ ሀይሉ ሰብሳቢ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደተናገሩት በከተማዋ የምርት አቅርቦትን በሚፈለገው ልክና አግባብ ከፍ ከማድረግ፤ ህግና ስርዓትን የተከተለ ጤናማ የግብይት ስርዓትን ከማስፈን አንዲሁም ወቅታዊ የግብይት ስርዓት መሠረት ያደረገ የመረጃ ተደራሽነት ከማስፋት አኳያ ተጨባጭ ዉጤታማ ስራዎች መሠራቱን ጠቅሰዉ ለዉጤቱ መሳካት ከማዕከል አሰከ ወረዳ እንዲሁም ከአጎራባቾቻችን ከተሞች ጋር በየደረጃዉ ያለዉ አመራር ተቀናጅቶ በሙሉ አቅሙ መስራት በመቻሉ ነዉ ብለዋል።

ባለፉት ስድስት ወራት የምርት እጥረትና የዋጋ ንረት እንዳይፈጠር፣ የኩፖን ስርጭት በመጀመር፣ በኮሪደር ልማት የተነሱ የሸማች ሱቆችን ምትክ በመስጠት፣ ህገወጥነትን በመቆጣጠርና በመከላከል፣ የሚዲያ ሽፋን በመስጠት፣ የገቢ አሰባሰብ ስራን በማጠናከር፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያ በማስፋት እንዲሁም ግብረ ሀይሉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራቱ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመላክቷል።

የግብረ ሀይሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተሰሩ ስራዎች በህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ላይ እሴት የሚጨምሩ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ ወራቶች የተሻለ ስራ ለመስራት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የመሰረተ ልማትና ተያያዥ ጥያቄዎችን በመመለስ፣ በኮሪደር ልማት ለፈረሰባቸው ሸማች ማህበራት ምትክ ቦታ በመስጠት እና ምርት ለመከዘን የሚያስችል ቦታ ማዘጋጀት በአንድ ተቋም የሚፈጸም ባለመሆኑ ትኩረት በመስጠት በቅንጅት ተናበው እንዲሰሩ ጠይቀዋል።

በመጨረሻም የእቅድ ክለሳን በማድረግ፣ የምርት አቅርቦትንና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የሸማች ማህበራት በማጠናከር፣ የቁጥጥርና ህግን የማስከበር ስራ ማጠናከር፣ የገቢ አሰባሰብ ችግርን መፍታት እንዱሁም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት በቀጣይ ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት በመሆናቸው ግብረ ሀይሉ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments