
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የ6 ወር የስራ አፈፃፀሙን ከሠራተኞች እና ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ገመገመ፡፡
ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የ6 ወር የስራ አፈፃፀሙን ከሠራተኞች እና ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ገመገመ፡፡
============================
አዲስ አበባ፣ ጥር 24 ቀን 2017ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የ6 ወር የስራ አፈፃፀሙን ከሠራተኞች እና ከክፍለ ከተማ አመራሮች ጋር ገመገመ፡፡
በዛሬው ዕለት በተካሄደው በዚሁ የበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ውይይት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ም/ ቢሮ ኃላፊ አ/ቶ ፍሰሀ ጥበብ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡
አክለውም ቢሮው በግማሽ ዓመቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የነበሩ ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር፣ ገበያ ማረጋጋት እንዲሁም ቢሮው በመደበኛ ተግባራት በያዛቸው እቅዶች አፈፃፀም የተሻለ አፈፃፀሞች ለማስመዝገብ መቻሉ ገልፀዋል፡፡
ጨምሮም የንግድ ቢሮ የንግድና ሬጉላቶሪ ኢንስፔክሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ወ/ሪ ቅድስት ስጦታው የሚካሄዱ የቁጥጥር ስራዎች መደበኛ የንግድ ተቋማት፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም የገበያ ማዕከላትን ትኩረት ያደረጉ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በዛሬው እለት በተካሄደው የውይይት መድረክ የቢሮው የበጀትና እቅድ ዳይሬክቶሬት አቶ መለሰ ባህሩ ሪፖርት እና የ2017ዓ.ም ቀሪ ወራት ዕቅድ ያቀረቡ ሲሆን ከቤቱ ለተነሱ ሃሳቦች በቢሮው አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ተጠናቋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments