
የንግድ ምዝገባ ፍቃድ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የተገልጋይ እርካታን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
የንግድ ምዝገባ ፍቃድ አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የተገልጋይ እርካታን ለማሻሻል እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
አዲስ አበባ ጥቅምት 27/2017 ዓ.ም
ዛሬ በማዕከልና በክፍለ ከተማ ደረጃ ለሚገኙ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ ደንበኞች አገልግሎት ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍሰሀ ጥበቡ ዘርፉ ባለፉት አመታት ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ በመተካት አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።አገልግሎቱ ሲሰጥ የነበረው ከወረዳ ጀምሮ እንደነበር አስታውሰው ቢሮ ባደረገው ሪፎርም ተግባሩ በቢሮ ደረጃና በክፍለከተማ ብቻ እንዲሰራ ለማስቻል ሰራተኞችን በአዲስ መልክ እንዲደራጁ በማድረግ በጥናት በተለዩ የስልጠና ርዕሶች ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጣቸው እንደሚገኝ ገልፀዋል።
ስልጠናው ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በተገልጋይ አያያዝ፣በስራተኛ ስነምግባር፣በኦን ላየን ሲስተም አጠቃቀም እና በንግድ ምዝገባና ፍቃድ አዋጅ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments