ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና...

image description
- In ንግደረ    0

ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ

ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ::

አዲስ አበባ፤ ጥር 29/ 2017 ዓ.ም

ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ማህበራት ኤግዚቢሽንና ባዛር "የህብረት ስራ ማህበራት ሚና ለኢትዮጵያ ብልጽግና" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጃንጥራር አባይ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሰለሞን ላሌ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ(ዶ/ር)፣ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ማህበራት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ፣ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ ከ350 በላይ የግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ተሳትፈውበታል።

በመርኃ ግብሩ ከ110 በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች የሚቀርቡ ሲሆን ከ70 ሺህ በላይ የመዲናዋ ነዋሪዎች ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።

በመድረኩ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ግብይት እንደሚፈጸምና ማህበራት ምርታቸውን ከማስተዋወቅ ባሻገር የገበያ ትስስር እንደሚፈጥሩበት ተመላክቷል።

የመርኃ ግብሩ አካል የሆነው ሲምፖዚየም ትናንት በስካይ ላይት ሆቴል መካሄዱ ይታወሳል።

ኤግዚቢሽንና ባዛሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ11ኛ ጊዜ፤ በከተማ ደረጃ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን እስከ የካቲት 3 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments