የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በቀጣይ ትኩረት ተሰጥ...

image description
- In ንግደረ    0

የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ በሚተገበሩ ጉዳዮች ላይ ውይይ አደረጉ፡፡

የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ በሚተገበሩ ጉዳዮች ላይ ውይይ አደረጉ፡፡

አዲስ አበባ:- የከቲት 6/6/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አመራርና ሰራተኞች በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ላይ ቀጣይ ትኩተረት ሊሰጣቸው እንደሚገቡ አቅጣጫ በተቀመጠባቸው ነጥቦች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዛሬዉ ዕለት ለቃላችን እንታመናለን የጉባኤ አቅጣጫዎችን ተፈፃሚ እናደርጋለን በሚል ጉባኤው በወሰናቸው እና በመንግስት መዋቅሩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲተገበሩ የተቀመጡ 10 ዋና ዋና ነጥቦች የቢሮው አማካሪ አቶ ስመኘው ተሾመ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን እንደ ንግድ ቢሮም ሁኔታዎችን በቅጡ በመረዳት እና እርስ በእርስ በመደጋገፍ አንዱ አንዱን በማብቃት በጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አላማቸውን እንዲያሳኩ በትጋት መስራትና አገልጋይነትን በተግባር መግለጽ እንዲሁም አገልግሎትን ማዘመንና ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም በጽንዎት ሰጥተው አንስተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮ ፅ /ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ የዛሬው ስብሰባ ዋናው አላማ ውሳኔውን ከሲቨል ሰርቪሱ አካላት ጋር የመግባባትና ግንዛቤ መያዝ እንድንችል ያለመ መሆኑ አስረድተው አቅጣጫዎቹ በአገልግሎት ዘርፉ ቀጣይነት ያለው ለውጥ እና ውጤት በማምጣ የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ ለማረጋገጥ ወሳኝ በመሆናቸው ቤደረጃው የሚገኘው የተቋሙ አመራርና ሰራተኛም ይህንኑ እውን ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚጠበውበት አሳስበዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments