ቢሮው በመንግስት ድጋፍ የአጋር ባለሀብቶች ዳቦ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው በመንግስት ድጋፍ የአጋር ባለሀብቶች ዳቦ ፋብሪካዎች ወቅታዊ ተግባራት አፈፃፀም ላይ ሪፖርት አቀረበ ።

ቢሮው በመንግስት ድጋፍ የአጋር ባለሀብቶች ዳቦ ፋብሪካዎች ወቅታዊ ተግባራት አፈፃፀም ላይ ሪፖርት አቀረበ ።

=========================

አዲስ አበባ ፡-የካቲት 7 /2017 ዓ/ም

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በመንግስት ድጋፍና የአጋርነት(Public Private Partnership) በግል ባለሀብቶች የተገነቡ ዳቦ ፋብሪካዎች ወቅታዊ ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂዷል ፡፡

በዛሬው እለት በተደረገው ውይይትም የቢሮው ግብይትና ገበያ ልማት ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ ካሳሁን በየነ በመስክ ጉብኝት የተገኘውን ሪፖርት በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የቢሮው የህግ አገልግሎት ቡድን ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ ተገኑ እንደገለጹት ባለሀብቶቹ የገቡትን ውል በአግባቡ እንዳልተወጡ ተናግረው ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችልና ባለሀብቱን የሚደግፍ ውል ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን ባለ ሀብቶቹ በዚህ ማሻሻያ መነሻነት የተሻለ ምርት አቅርቦት ላይ ውጤት ሊያመጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በመጨረሻም የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በመንግስት ደረጃ ህብረተሰቡን ይደግፋሉ ተብለው ለባለሀብቶቹ የተሰጡትን ሰፋፊ መሬቶች ላይ ሌላ ተጨማሪ እንደ እንጀራ ፤የሰብል ምርት፤ ወፍጮ ቤት፤ ልኳንዳ አገልግሎቶችን አካተው በመሥራት ንግዳቸውን እንዲያስፋፉ እና ከመንግስት ጋር በገቡት ውል መሠረት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ማምረትና አገልግሎታቸውን እንዲያቀርቡ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል ፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments