ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ...

image description
- In ንግደረ    0

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ ያስመዘገባቸዉ ስኬቶች ማሳያዎች፤-

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት 6 ወራት በንግዱ ዘርፍ ያስመዘገባቸዉ ስኬቶች ማሳያዎች፤-

የንግድ ምዝገባና ዕድሳት በተመለከተ 23,064 አዲስ የንግድ ምዝገባ አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዞ 31,267 መሰጠት መቻሉ እንዲሁም 46,002 አዲስ የንግድ ሥራ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት እቅድ ተይዞ 53,576 መስጠት የተቻለ ሲሆን ለ411,548 የንግድ ሥራ ፈቃድ እድሳት አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 285,622 መፈፀም ተችሏል፡፡

ከንግድ ቁጥጥርና ክትትል አኳያም በህገ-ወጥ የንግድ ሥራ ተሰማርተው ከተገኙ 14,129 ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ወደ ህጋዊነት መመለስ ተችሏል፡፡

በተጨማሪም በኮንትሮባንድ እና በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተያዘ መሰረታዊ ሸቀጥ እና ነዳጅ ምርት 18,985 ሊትር ቤንዚን፣ 9,434.5 ሊትር ናፍጣ፣ 189 ሊትር ኬሮሲን፣ 964,324 ሊትር ዘይት እና ቡና 48 ኬሻና 100 ኪሎ ግራም በመያዝ በአጠቃላይ 29,305,804.6 (ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሶስት መቶ አምስት ሺ ስምንት መቶ አራት ብር) ብር ለመንግስት ገቢ ተደርጓል፡፡

የእሁድ ገበያ መዳረሻዎችን በማድረስ፤እንዲሁም ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማድረግ በተሰራዉ ስራ የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱን እንዲያጥር በማድረግ እና አቅርቦትን በማሳለጥ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ለመቀነስ ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል በመንግስት በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች አኳያ 149,532 ኩ/ል የስኳር ምርት፤ 2,195,569 ሊትር የምግብ ዘይት በተፈጠረዉ ትስስር ለንግድ ኮርፖሬሽና ለህብረት ሥራ ኤጀንሲ ማሰራጨት ተችሏል፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments