ቢሮው በመዲናዋ የምርት ዋጋን ለማረጋጋት ቀጥታ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው በመዲናዋ የምርት ዋጋን ለማረጋጋት ቀጥታ የግብይት ትስስር የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው።

ቢሮው በመዲናዋ የምርት ዋጋን ለማረጋጋት ቀጥታ የግብይት ትስስር የመፍጠር ስራ እየተሰራ ነው።

=========================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ፡-የካቲት 15 /2017 ዓ/ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በመዲናዋ የምርት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት አርሶ አደሮች ምርታቸውን በገበያ ማዕከላትና በእሁድ ገበያ ቀጥታ እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነው ሲል የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የፍጆታ ምርት ለሸማቾች ማቅረብ የሚያስችል ስምምነት ከ19 አርሶደሮችና አምራቾች ጋር ተፈራርሟል።

በስምምነቱ የንግድ ቢሮ የግብይትና ልማት ሀለፊ ፍስሀ ጥበቡ፤ አርሶ አደሮችና አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ በተገነቡ ማዕከላት፤ በቅዳሜና በእሁድ ገበያ እንዲሁም በሱቆች ለሸማቾች ተደራሽ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል።

ስምምነቱ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን በቀጥታ በገበያ ማዕከላት፥ በቅዳሜና በእሁድ ገበያና በሱቅ ለሸማቾች ተደራሽ በማድረግ የምርት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ይጠቅማል ብለዋል።

ስምምነቱ ደላሎችን ከገበያ ሰንሰለቱ የሚያስወጣ፤ ሸማቹንና አርሶ አደሩን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደረግ ነው።

አርሶ አደሮችና አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ ለሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እንዲያደርጉ የገበያ ማዕከላት፤ የእሁድ ቅዳሜ ገበያ ቦታና ሱቆች ዝግጁ ተደርገዋል ሲሉ አብራርተዋል።

አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ ለሸማቹ ተደራሽ ማድረጋቸው ተጠቃሚነታቸውን ስለሚያሳድግ ምርትና ምርታማነትን ያሳድጋል ሲሉ ገለጸዋል።

በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን ለሸማቹ በቀጥታ እያቀረቡ ነው፤ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍያ ያሉ አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ ለሸማቹ እንዲያቀረቡ የሚያስችል ስራም ተሰርቷል፤ ማቅረብ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments