ቢሮው ከቁም እንስሳት ነጋዴዎች ጋር ውይይት አካ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው ከቁም እንስሳት ነጋዴዎች ጋር ውይይት አካሄደ

ቢሮው ከቁም እንስሳት ነጋዴዎች ጋር ውይይት አካሄደ

============================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የካቲት 20/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ በተቋቋሙ የቁም እንስሳት መሸጫ የገበያ ማዕከላት ግብይት ከሚያካሂዱ የነጋዴዎች ማህበር አመራሮች ጋር ውይት አካሂዷል፡፡

ለውይይቱ መነሻ ሪፖርት በቢሮው የገበያ ማዕከላት አስተዳዳር ዳይሬክተራ አቶ ደበሬ ዲንሳ የቀረበ ሲሆን የቢሮው ምክትል ኃላፊና የግብይት እና ገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊው አቶ ፍስሀ ጥበቡ በዘርፉ የሚስተዋሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶችን በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በግብይት ሂደቱ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ማረም በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም የከተማው ደንብ ማስከበር እና የፖሊስ መዋቅር ተወካዮችም ዋና ዋና ተግዳሮቶችን አንስተው፡፡

የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማህበር አመራሮች በበኩላቸው ህገ-ወጥ ተግባራቱን በማስተካከል ሂደት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ገልጸው በቢሮው ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ጉዳዮችንም አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ውይይቱን የመሩት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የቁም እንስሳት ገብይቱ የተረጋጋ እና ህግና ስርዓትን በጠበቀ አግባብ እንዲመራ ቢሮው በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው በተለይም ከገበያ ማዕከላት ውጪ የሚደረግ ግብይት፤ ህገ-ወጥ ደላሎችንና ከክልል ንግድ ፈቃድ ወስደው አዲስ አበባ ላይ ግብይት የሚያካሂዱ ነጋዴዎች በምን አግባብ መስራት እናዳለባቸውን በቀጣም በዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ማብራሪያና የስራ ስምሪት በመስተት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments