ቢሮው ሁለት ደንቦችን አጸድቆ ተግባራዊ ማድረግ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው ሁለት ደንቦችን አጸድቆ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ ፡፡

ቢሮው ሁለት ደንቦችን አጸድቆ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ ፡፡

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በከተማዋ የሚከናወነውን የንግድ ስርዓት ህጋዊነትን የተከተለና ከተማዋ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የሚመጥን እንዲሆን የመሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሆነ ገልጾ ከእነዚ ዘርፈ ብዙ ተግባት መካከልም በቅረቡ በአዲስ አበባ ካቢኔ የጸደቁ ሁለት ደንቦችን ላይ ከተቋሙ አመራሮች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡ በመዲናዋ የሚገኙ የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እስከምሽት 4፡00 ሰዓት አግልግሎት እንዲሰጡ የሚደነግገው ደንብ የመጀመሪያው ሲሆን ሁለተኛው ወደ ተግባር እንዲገባ ውይይት የተደረገበት ከመደበኛ ንግድ ስርዓት ውጪ ሆነው የንግድ ስራን የሚያከናውኑ ነጋዳዎች ህጋዊ ስርዓት ባለው አግባብ ደንብና መመሪያን በተከተለ ተከትለው የሚነግዱበትን ሥርዓት የሚደነግጉ ደንቦች ናቸው፡፡

በውይይቱ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሁሉም ክፍለ ከተማ የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የማዕከል ዳይሬክተሮች የተገኙ ሲሆን ደንቦቹን ወደ ተግባር በመለወጥ ሂደት ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፤ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በየደረጃው ያለው አመራር ደንቦቹ ውጤታማ ለማድረግ በቅድምያ ደንቦቹን ለንግዱ ማህበረሰብ የማስተዋወቅና ግልጸኝነት የመፍጠር ስራ ትኩረት ተሰጥቶ በቀጣይ ቀናት ከወረዳ እስከ ማዕከል እንዲተገበር አሳስበው የንግዱ ማህበረሰብ የደንቦቹን ዓላማ በአንክሮ በመረዳት ለተግባራዊነቱ በጋራ መስራት እንደሚጠበቅበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments