
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ማስፋፊያና ቀሪ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው በሙሉ አቅም አገልግሎታቸውን እንደሚቀጥሉ ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ማስፋፊያና ቀሪ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው በሙሉ አቅም አገልግሎታቸውን እንደሚቀጥሉ ተገለጸ።
=============================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 05/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስገነባቸው የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ላይ ያልተጠናቀቁ ቀሪ ግንባታዎች እና አዲስ እየተገነቡ የሚገኙ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት ምቹ ሁኔታን በሚፈጠርበት ሁኔታ ላይ የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች ከሜጋ ፕሮጀክቶች ጸ/ቤት ከኦቪድ ኮነስተራክሽን አመራች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
የንግድ ቢሮ ሀላኃፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጂ እንደተናገሩት ቀደም ብለው ተገነቡ እና ወደ አገልግሎት የገቡ የገበያ ማዕከላት ያልተሟሙላቸው ግብዓቶች ለአብነትም ማሞቂያ፣ ማቀዝቀዣ የካሜራ ገጠማና መሰል የማጠቃለያ ስራዎች በተቻለ ፍጥነት መጠናቀቅ እንዳለባቸውን ግንባታቸው በሂደት ላይ የሚገኙ የገበያ ማዕከላትንም ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለአገልግሎት ማብቃት አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ግንባታውን በማከናወን ላይ የሚገኙ ተቋማት አመራሮችም የቢሮ ኃላፊዋ ያነሷቸው ነጥቦች ተገቢ መሆናቸውንና በቀጣይ ሶስት ወራት የማዕከላቱን የግንባታና ግብዓቶችን የማሟላት ስራ ለማጠናቀቅና ለማስረከብ እንደሚተጉ አሳውቀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments