የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ አክሲዮን ማህበራት ጋር በንግድ ቦታቸው መልሶ ማልማት ላይ ውይይት አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ አክሲዮን ማህበራት ጋር በንግድ ቦታቸው መልሶ ማልማት ላይ ውይይት አድርገዋል።

=======================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 09/2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የንግድ አክሲዮን ማህበራት ጋር የንግድ ቦታቸው መልሶ ማልማት ላይ ውይይት አድርገዋል።

በዛሬው እለት በተካሄደው ውይይት በቀደሙ ዓመታት ከ60 በላይ የንግድ አክሲዮን ማህበራት የማልማት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን መረጃውን ያጣሩት የአክሲዮን ማህበራት ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ ወ/ሮ እልፍነሽ ጌታሁን በንግድ ማህበራቱ በኩል ማሟላት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በአግባቡ አሟልተው መቅረብ አለመቻላቸውን በሪፖርታቸው ያቀረቡ ሲሆን በተለይም ማህበራት አባላቶቻቸው የንግድ ፍቃድ ያላደሱ ወይም የሌላቸው፣ የኦዲት ሪፖርት አለማቅረብ፣ የተመዘገበ ካፒታል እና ተዛማጅ ሰነዶች ተናባቢ አለመሆን፣ የውርስ ሂደትን በሚመለከተው የህግ አግባብ አለማጠናቀቅ በጉልህ የተስተዋሉ ጉድለቶች መሆናቸውን በዝርዝር አቅርበዋል።

በውይይቱ ሂደት የአክሲዮን ማህበራት አሉብን ያሏቸውን ችግሮች ለቢሮው ኋላፊዎች አቅርበዋል። በተነሱ ጉዳዮች ላይ ምላሽ የሰጡት የቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ፍስሀ ጥበቡ በዘርፉ በኩል ለአክሲዮን ማህበራት የሚደረገው ክትትል እና ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው የአክሲዮን ማህመራቱ በተደረገው መረጃን የማጣራት ስራ የተገኙ ጉድለቶችን እስከ ሚያዝያ 30/2017 ዓ.ም ድረስ እንዲያሟሉ አሳስበው ከዚህም በተጨማሪም የአክሲዮን አባል ሆነው ንግድ ፈቃድ ያላደሱ ወይም የሌላቸው አካላትን ወደ ህጋዊ አሰራር ለማምጣት በጋራ መሥራት እንደሚገባ አስታውቀዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ለተነሡ ጥያቄዎች ማብራሪያና የማጠቃለያ ሀሳበቦችን ያቀረቡ ሲሆን በተለይ የከተማ አሰተዳደሩ የአክሲዮኖችን ጥያቄ ምላሽ ለመሥጠት በተደጋጋሚ ጊዜ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ማህበራቱ በህግና መመሪያዎች በግልጽ የተቀመጡ አስገዳጅ ሰነዶችን በሚገባ አሟልተው አለማቅረብ ትልቅ እንቅፋት ፈጥሮ የቆየ መሆኑን እና አሁን ላይ በተደረገው ማጣራት የታዩ ጉድለቶችን በፍጥነትና በጥራት አሟልተው ለቢሮ እንዲያቀርቡ አሳስበው ውይይቱ ተጠናቋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments