ቢሮው በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣ ደንብ ቁጥር185/2017 ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።

ቢሮው በምሽት የንግድ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የወጣ ደንብ ቁጥር185/2017 ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አሁን ከደረሰችበት ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ለውጥ አንፃር

የአብዛኛው ማህበረሰብ የሥራ ባህል እና ፍላጎት በመለወጡ የንግድ ሥራዎችንና

አገልግሎቶችን በምሽት መከወን እየተለመደ የመጣውን ተግባር ወጥነትና ቀጣይነቱን

ማረጋገጥ በማስፈለጉ እና በከተማዋ በስፋት እየተከናወነ የሚገኘው መሠረተ-ልማት በኢኮኖሚው ላይ የፈጠረውን መነቃቃት አጠናክሮ ለማስቀጥል፣ የስራ ባህልን ይበልጥ ለማዳበር ፣ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት

በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበት

ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ደንቡ መውጣቱን አንስተው ይህ ደንብ ቀደም ብሎ በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ያስተላለፈውን ውሳኔ ለማስፈጸም በመሆኑ ከዛሬ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሐቢባ ሲራጅ ለቢሮው ኮሙኒኬሽን አብራርተው በደንቡ የተካተቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ማብራሪያ በሁሉም የሚዲያ አውታሮች አማካኝነት ማህበረሰቡ እንዲያውቃቸው እንደሚደረግ እና ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራም አክለው ገልጸዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments