
ኢትዮጵያ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው
ኢትዮጵያ የምርት ጥራትን ለማረጋገጥ እየሰራች ነው
=============
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 10/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተበባር በዓለም ለ42ኛ በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጌዜ የሚከበረውን የዓለም የሸማቾች ቀን "ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለሸማቾች" በሚል መሪ ሀሳብ እያከበረ ነው።
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሀላፊ ሀቢባ ሲራጅ እንደገለጹት፤ በሀገሪቱ የሸመቾችን መብት ለማስጠበቅ የሚረዳ አዋጅ ከወጣ ጀምሮ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል።
አምራቹ ጥራቱን የጠበቀ ምርት እንዲያቀርብ እና ሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገዙ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የንግድና ሸማቾች ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሊቁ በነበሩ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት የምታቀርባቸውን ምርቶች ጥራት ለማስጠበቅ የጥራት መንደር አቋቁማ እየሰራች ትገኛለች።
በሸማቹ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት በመከላከል ረገድ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments