
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለሞዴል ነጋዴዎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለሞዴል ነጋዴዎች እውቅናና ሽልማት ተበረከተ።
================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 11/2017 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት በግማሽ ዓመቱ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የወረዳ ጽ/ቤቶችና ለሞዴል ነጋዴዎች እውቅና ሰጥቷል።
በእውቅና አሰጣጡ በክብር እንግድነት የተገኙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው አዲስ ከተማ ትልቅ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድበት መርካቶ የሚገኝበት በመሆኑ በልዩ ሁኔታ እንደሚታይ ገልፀው በተለይም በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ የምትገኝዋን አዲስ አበባን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ነጋዴው ማህበረሰብ በነቃ ሁኔታ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንዳለ ተናግረዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበኩላቸው እንደ ክፍለ ከተማ ነጋዴው ማህበረሰብ ህግና ስርዓትን አክብሮ እንዲሰራና በማህበረሰቡ የሚታዩ የኑሮ ውድነት ችግሮችን እንዲያቃልል እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በተለይም ትክክለኛ ፍታዊ የንግድ ስርዓት እንዲሰፍን ተቀራርበን መስራታችን አጠናክረን እናስቀትላለን ሲሉ ገልፀዋል።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙስጠፋ ቱኩ በበኩላቸው ለሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ልማት የንግዱ ማህበረሰብ ድርሻ ወሳኝ በመሆኑ ታማኝና ሞዴል ነጋዴዎችን ማበረታታት ተገቢ ነው ብለዋል::
የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ይድነቃቸው ግርማ በበኩላቸው ሞዴል ነጋዴዎችን በተመለከተ መስፈርቶች የተለዩ ሲሆን በዚህም ንግድ ፈቃድ በወቅቱ የሚያድሱ፣ የንግዱን ህግ አክብረው የሚሰሩ፣ ሰው ተኮረት ስራ ላይ በንቃት የሚሳተፉ፣ ለ50 ሰው እና ከዚያ በላይ የስራ እድል የፈጠሩ፣ ተገቢውን የመንግስት ግብር በወቅቱ የከፈሉ እና የንግድ ተቋማቸውን በቴክኖሎጂ ያዘመኑ ሞዴል ነጋዴዎች የተሸለሙ መሆናቸውን ገልፀዋል::
በተጨማሪም በ2017 ዓ.ም በ6 ወር ምዘና የተሻለ ውጤት ያመጡ ወረዳዎች እና ሰራተኞች ባለድርሻ አካላት የተሸለሙ ሲሆን በዚህም መሰረት፡-
1ኛ ደረጃ ወረዳ 1 ንግድ ጽ/ቤት
2ኛ ደረጃ ወረዳ 12 ንግድ ጽ/ቤት
3ኛ ደረጃ ወረዳ 10 እና 9 ንግድ ጽ/ቤት የእውቅና ሰርተፊኬትና ዋንጫ ተበርክቶላቸዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments