
ቢሮው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ስርዓት ለማስያዝ እየሰራ መሆኑን ገለፀ
ቢሮው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ስርዓት ለማስያዝ እየሰራ መሆኑን ገለፀ
===================
አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 11/2017 ዓ/ም
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ስርዓት ለማስያዝ እየሰራ መሆኑን ገለፀ::
መደበኛ ያልሆነ ንግድ ፈቃድ አመቻች ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ተሰማ ጨመዳ ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት በከተማችን ውስጥ በተፈቀዱ ጎዳናዎች ፤አደባባዮች፤የተለያዩ ቦታዎች ላይ የንግድ ስራ እንዲሰሩ የተፈቀደላቸው የከተማ ነዋሪዎች ፤ንፁህና እና በከተማ ደረጃ አኳያ እንደሚሰማሩና ፈቃድ እንደሚወስዱ ማስቻላቸውን ተናግረዋል ፡፡
አክለውም መደበኛ ያልሆነ ነጋዴ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ መሰረት የልተመዘገበ እንዱሁም የንግድ ፈቃድ የሌለው መደበኛ ያልሆነ ንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ወይም ለመሰማራት የሚፈልግ እስከ ብር 100.000.00 አንድ መቶ ሺህ ካፒታል ያለው እና ደንብ አክብሮ የሚሰራ ፈቃዱን እንደሚያገኝ ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments