የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ንግድ ቢሮ ኃላፊ...

image description
- In ንግደረ    0

የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ በመርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ደርሶባቸው በመሰራት ላይ የሚገኙ የንግድ ሱቆችን ጎበኙ።

የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ በመርካቶ ሸማ ተራ የእሳት አደጋ ደርሶባቸው በመሰራት ላይ የሚገኙ የንግድ ሱቆችን ጎበኙ።

================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 12/2017 ዓ/ም

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መሐል መርካቶ በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ በስፍራው ላይ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩትን ነጋዴዎች መልሶ ለማቋቋም የከተማ አስተዳደሩ በመስራት ላይ ይገኛል። ስራዎቹ ያለበትን ደረጃም የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ በመርካቶ ሸማ ተራ በመሰራት ላይ የሚገኙ የንግድ ሱቆችን ጎብኝተዋል።

የከተማ አስተዳዱ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ጉዳት የሚደርስባቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳዳር ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሃቢባ ሲራጅ በመርካቶ በደረሰው የእሳት አደጋ ለተጎዱ የንግድ ማህበረሰብንም መልሶ ለማቋቋም እየተሰራ ነው ብለውል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል በበኩላቸው የሱቆቹ ግንባታ በፍጥነት ተጠናቆ ነጋዴዎቹ ወደ ስራ እንዲገቡ እየሰራን ነው ብለዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments