ቢሮው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ የሚያስተገብር ግብረ- ሀይል ወደ ተግባር ገባ።

ቢሮው መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ የሚያስተገብር ግብረ- ሀይል ወደ ተግባር ገባ።

==========================

አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድን ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ የሚያስተገብር ግብረ- ሀይል ወደ ተግባር ገባ።

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ፣ መምጣቱን እና በመደበኛው የንግድ ሥርዓት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን በመገንዘብ ይህንን ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን የጠቀሱት የግብረ-ሀይሉ ሰብሳቢ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ክ ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ በሥርዓት ካልተመራ በከተማ ውበትና ገጽታ፤ በከተማ ጽዳት፤ በትራፊክ ፍሰትና እንቅስቃሴ፤ በኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት እና በከተማዋ ሰላምና ፀጥታ አጠባበቅ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል መሆኑ ታሳቢ ያደረገ እና ወደ ህጋዊ የንግድ ስርዓት መመለስ የሚያስችለው ደንብ ከወረዳ እስከ ማዕከል ላሉ የግብረ -ሀይል አባላት የስራ ስምሪት እና የቀጣይ አንድ ወር ዕቅድ ወጥቶ ውይይት በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments