ትናንት፤ ዛሬና ነገን ለኢትዮያ ልዕልና ፤ በሚል መሪ ቃል የቢሮ አመራር እና የመንግስት ሰራተኞች የ ዉይይት አካሄዱ
ትናንት፤ ዛሬና ነገን ለኢትዮያ ልዕልና ፤ በሚል መሪ ቃል የቢሮ አመራር እና የመንግስት ሰራተኞች የ ዉይይት አካሄዱ
አዲሰ አበባ መጋቢት 19/2017 ዓ.ማ
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ንግድ ቢሮ ትናንት፤ ዛሬና ነገን ለኢትዮያ ልዕልና ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር በተዘጋጀው ሰነድ ዉይይት ተካሄዳል፡፡
በዛሬ ዕለት ሰነዱን ያቀረቡት አቶ ዳንኤል ሚኤሳ የቢሮ የሰዉ ሀበት ልማት አሰተዳደር ዳይሬክተር ሲሆኑ የመጋቢታዊያን የለዉጥ ፈሬዎችና የነገ ተሰፈዎች በሚል ለውይይት የቀረበውን መነሻ ሀሳቦች በገለጻ አብራርተዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊዎች ለመድረኩ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን ከመድረኩ ምልሽ ተሰጥተቸዋል፡፡በዕለቱ የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡት የቢሮ ጽ/ቤት ጋላፊ አቶ ታረቀኝ ገመቹ እና አቶ ስመኘው ተሾመ የቢሮ አማካሪ ሲሆኑ እንደ ሃገር እነዚህን ለውጦች ለማስቀጠል የብሄራዊነት ገዢ ትርክት ግንባታን በማጠናከር ቅቡልነት ያለው ጠንካራ ሀገረ መንግሥት እውን ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተገኙ ለውጦችን በሁሉም አካባቢዎች ማስፋትና ማስቀጠል እንደሚገባ ለዚህም መላዉ ሰራተኛ በትጋትና በቁርጠኝነት እየተካሄደ ያለውን ልማት ማገዝና መስራት እንደሚጠበቅበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments