ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው የናፍጣ አ...

image description
- In ንግደረ    0

ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው የናፍጣ አቅርቦት እጥረት በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ አስታወቀ

ቢሮው በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው የናፍጣ አቅርቦት እጥረት በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ አስታወቀ

==========================

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ መጋቢት 29/2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የተፈጠረው የናፍጣ አቅርቦትእጥረት ለመፍታት እንዲቻል ባለሁት ቀናቶች ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን እና ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር የጋራ ግብረ-ኃይል በማቋቋም በሁሉም ማደያዎች የቁጥጥር ስራ ሲሠራ ቆይቷል፤ በዛሬው ዕለት የንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ በተገኙበት ነዳጅን ለማሰራጨት ኃላፊነት ከወሰዱ 20 ኩባንያዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱም ከተደረገው ክትትል መነሻነት ነዳጅን ወደ ሀገር ከማስገባት አኳያ ምም ዓይነት ጉድለት አለመኖሩን እና አሁን ላይ ያጋጠመው የናፍጣ እጥረት መነሻው ኩባንያዎች ለከተማዋ የተመደበውን የናፍጣ መጠን ለማደያዎች ወቅቱን ጠብቀው ማሰራጨት ላይ መሆኑ መረጋገጡን እና ይህም ባፋጣኝ መስተካከል እንደሚገባው የሥራ ኃላፊዎቹ አጽንዎት ሰጥተው አንስተዋል።

የኩባንያ ተወካዮችም ግኝቱ ትክክል መሆኑን እና ባጭር ጊዜም የናፍጣ አቅርቦቱ ወደነበረበት በቂ መጠን እንደሚመልሱ መግባባት ላይ ተደርሷለ።

በመንግስት ደረጃም ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት እንዲቻል ከአዋሽ መጠባበቂያ ናፍጣ ለሁሉም ማደያዎች በመሠራጨት ላይ ሲሆን ቅዳሜ እና ዕሁድ ላይ የነበረው ከ700,000 የነበረው የናፍጣ መጠን በዛሬው ዕለት 1.89 ሚሊየን ሊትር ለማደያዎች ለማሠራጨት መቻሉን እና በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት እጥረቱ ሙሉ በሙሉ ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን የንግድ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ አስታውቀው በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላትም አቅርቦቱ ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments