ለፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የምርት...

image description
- In ንግደረ    0

ለፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ቅድመ ዝግጅት እተደረገ ነው፡፡፡

ለፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ቅድመ ዝግጅት እተደረገ ነው፡፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሚያዘያ 2/2017ዓ.ም

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በቀጣይ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የፋሲካ በዓል የምርት እጥረት እና የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት በመደረግ ላይ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተግባሩ ያለበት ደረጃ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ላይ አዲስ አበባ ላይ የምርት አቅርቦት ላይ የሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት እና እነዚህን የመደገፍ እና የመቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

በእስካሁኑ ዝግጅት በቁም እንስሳት፣ በሰብል ምርቶች፡ በዶሮ እና እንቁላል አቅርቦት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራት ላይ መሆኑን ተሳታፊዎች ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ይህም ተግባር ቀደም ብሎ መጀመሩ ባዓሉ ቢቃረብበት ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን የአቅርቦት እጥረትና ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል እንደሚያስችል ተነስቷል፡፡

ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ተቋማቱ እያከናወኑ ያለው ተግባር ጥሩ ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል ገልጸው በዓሉ በሚቃረብበት ወቅት ሁሉም የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እና የግብርና ምርቶች መሸጫ ማዕከላት ሳምንቱን ሙሉ ክፍት እንደሚሆኑ እና በሌሎችም ገበያዎች በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖርና ግብይቱም የተረጋጋ እንዲሆን ጥብቅ ክትትል እና ቁጥጥር እንደሚደረግ ለዚህም ሁሉም ተቋማት በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments