Publications

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ያልሆነ የንግድ ሥራ ለመምራትና ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ…………………ገጽ ሺ፻፷፯

image description

ደንብ ቁጥር*8/2ሺ9
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ያልሆነ
የንግድ ሥራ ለመምራትና ሥርዓት ለማስያዝ
የወጣ ደንብ
በከተማችን በመካሄድ ላይ ያለው መደበኛ
ያልሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተስፋፋ በመምጣቱ በዘርፉ በርካታ ሰዎች
በተለይም ወጣቶችና ሴቶች ሲሳተፉበት
በመታየቱ፤
በዚህ አይነት የንግድ ሥራ ውስጥ የተሠማሩ
ዜጎች ለራሳቸው የሥራ ዕድል ፈጥረው
በመገኘታቸው እና የንግዱ አካሄድ የህጋዊ
ነጋዴዎችን ገበያ በማይሻማ መልኩ ሥርአት
በማስያዝ በቀጣይ ወደ መደበኛ የንግድ ሥርዓት
የሚሸጋገሩበት መንገድ ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ
በመገኘቱ፤

ዘርፉ በግብይት ሥርአቱ ውስጥ ሕጋዊ እውቅና
ተሰጥቶት በሥርዓት መምራት በማስፈለጉ፤
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተሻሻለው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ
ቁጥር 3)^1/፲፱፻(5 አንቀጽ @3ንዑስ አንቀፅ
(1) (ረ)እና በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር
አስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት
እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፴፭/፪ሺ፬
(እንደተሻሻለ) አንቀፅ ፹፬መሠረት ይህን ደንብ
አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌ
1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ ‹‹የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
መደበኛ ያልሆነ ንግድ ሥራ ለመምራትና
ሥርዓት ለማስያዝ የወጣ ደንብ ቁጥር
፹፰/፪ሺ፱ዓ.ም››ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
2. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው
ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡
1. ‹‹አስተዳደር››ማለት የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር ነው፤
2. ‹‹የንግድ ሕግ›› ማለት በ%2 ዓመተ
ምህረት የወጣው የንግድ ሕግ ነው፤
3. ‹‹አዋጅ›› ማለት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ
አዋጅ ቁጥር ፱፻፹/፪ሺ፰ ነው፤
4. ‹‹ቢሮ›› ማለት የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር የንግድ ቢሮ ነው፤
5. ‹‹የክፍለ ከተማ ጽሕፈት ቤት››ማለት
በአስተዳደሩ አደረጃጀት መሠረት
በሁለተኛ የእርከን ደረጃ የሚገኝ የንግድ
ጽህፈት ቤት ነው፤