አዋጅ ቁጥር 84/2016 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ
አዋጅ ቁጥር 84/2016
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የከተማው አስተዳደር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግስት እና በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በእኩልነት፣ በግልጽነትና በፍትሃዊነት መርህ መሠረት ለመፈጸም በሚያስችል መልኩ የከተማው አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባራቸውን እንደገና መወሰን በማስፈለጉ፤ በሀገራችን ብሎም በከተማችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ውጤታማ፣ ዘላቂና ተቋማዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 361/1995 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ (1) ተራ ፊደል (ሀ) መሰረት ይህንን አዋጅ አውጥቷል፡፡